የኮርስ መግለጫ ፡-
ይህ ኮርስ ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክር መርሆዎችና ልምምዶች መግቢያ ይሰጣል። ተማሪዎች መንፈሳዊና ፣ መሀበራዊ የህይወት ተግዳሮቶች ለሚያጋጥማቸው ግለሰቦች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ እና ስነልቦናዊ ምክር እንዴት መስጠት እንደሚችሉ ይስተምራል። ኮርሱ ወሰጥ የሚገኙት ርዕሶች የቅዱሳት መጻሕፍትን ሚና ፣ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ፣ የፅሎትን አስተዋፅኦ ከልብ የሆነ ማዳመጥ ፣ ርኅራኄ እንዲሁም ሀዘን ፣ ጭንቀት እና በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶችንና ችግሮችን ለመፍታት የሚረዱ ተግባራዊ ስልቶችን ያካተተ ነው።
የኮርሱ አላማ ፡–
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክር ማለት ምን ማለት እንደሆነና ባሉበት ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ጠቀሜታና አገልግሎት መግለጽ እንዲችሉ ብቁ ማድረግ።
በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክርና በዓለማዊ የምክር አገልገሎት መካከል ያለውን አቀራረብ እንዲያውቁ ያደርጋል።
ከምክር ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆች እንዲለዩ ማድረግ።
ለምክር አገልግሎት ውጤታማ የመግባቢያና የማዳመጥ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ማድረግ።
ግለሰቦች ለሚገጥሟቸው ልዩ ልዩ የሕይወት ፈተናዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን መተግብር እንዲችሉ ማብቃት።
የኮርሱ አጠቃላይ ዝርዝር (Course Outline)
ክፍል 1፥ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክር አገልግሎት መሰረታዊ ጽንሰ-ሐሳቦች
ክፍል 2፥ የሰው ልጅ ተፈጥሮ እና ችግሮች
ክፍል 3፥ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆች በምክር መስጠት ውስጥ
ክፍል 4፥ የምክር መስጠት ዘዴዎች እና ክህሎቶች
ክፍል 5፥ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት
ክፍል 6፥ የስነምግባር እና የሃይማኖታዊ ጉዳዮች
ክፍል 7፥ ተግባራዊ ስልጠና (Practical Training)
የኮርሱ ውጤት (Expected Outcomes)
በኮርሱ መጨረሻ ላይ ተማሪዎች፡
የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክር አገልግሎትን መሰረታዊ መርሆች ይረዱታል።
የሰዎችን ችግሮች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ እንዴት እንደሚመለከቱ ይማራሉ።
የምክር አገልግሎት ክህሎቶችን በተግባር ይተገብራሉ።
የስነምግባር እና የሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ይገነዘባሉ።
የኮርሱ ምድቦች
የክሬዲት ሰዓቶች፡ 3
የቀጥታ ክፍለ-ጊዜዎች፡ 1 በሳምንት (3ጊዜ በወር)
የጥናት ጊዜ፡ በሳምንት 3 ሰዓት
የተማሪዎች የዕውቀት ግምገማ ፡ ሳምንታዊ ጥያቄዎች ፣ በየወሩ የመጨረሻ ሳምንት ፈተና
የኮርሱ መጸሀፍ
Curriculum
- 7 Sections
- 22 Lessons
- 8 Weeks
Expand all sectionsCollapse all sections
- ክፍል አንድየመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክር አገልግሎት መሰረታዊ ጽንሰ-ሐሳቦች5
- ክፍል ሁለትየሰው ልጅ ተፈጥሮ እና ችግሮች3
- ክፍል ሶስትየመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክር አገልግሎት መርሆች3
- ክፍል አራትየምክር አገልግሎት ዘዴዎች እና ክህሎቶች4
- ክፍል አምስትየተለያዩ ችግሮችን መፍታት3
- ከፍል ስድስትየስነምግባር እና የሃይማኖታዊ ጉዳዮች3
- ከፍል ስባትተግባራዊ ስልጠና (Practical Training)3