የኮርሱ መግለጫ
ይህ ኮርስ መፅሐፍ ቅዱሳዊ እና ነገረ መለኮታዊ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ሥራውን በብሉይና በአዲስ ኪዳን መፅሐፍት አማካይነት የሚያስገነዝብ ጥናት ነው። ይህም የመንፈስ ቅዱስን መልኮትነት፣ አካልነት እና የፍጥረት፣ የመግለጥ፣ የድነት፣ የመቀደስ እና ለአገልግሎት የማስታጠቅ ሚናው የሚዳሰስበት ነው። በተጨማሪም ኮርሱ የመንፈስ ቅዱስን ሥጦታዎች፣ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ፣ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት በአማኙ ሕይወት፣ አምልኮ እና የቤተክርስቲያ አገልግሎት አሰራሩን የምናይበት ነው። ጤናማውን ትምህርት ከጤናማ የክርስትና ሕይወት እና የአገልግሎት ልምምድ አዋህዶ በአጥቢያ ሕብረት ውስጥ ለማቀርብ ጥረት ይደረጋል።
የኮርሱ ዓላማ:
የዚህ ኮርስ ግብ ተማሪዎች ጠንካራ መፅሐፍ ቅዱሳዊ እና ነገረመለኮታዊ የመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ሥራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ነው። በተጨማሪም ነገረ መንፈስ ቅዱስን በመረዳት መንፈስ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በፍጥረት፣ በመግለጥ፣ በድነት ፣ በመቀደስ እና ለአገልግሎት በመለየት እና ከሕይወት ጋር በማዛመድ በግል ሕይወታቸውን እድገት፣ ለሥነ ምግባር መሻሻል እና ለውጤታማ አገልግሎት ለመታጠቅ ነው።
የዚህ ኮርስ ግብ
የትምህርቱ ግብ
ይህን ኮርስ እንደሚገባ የሚያጠናቅቅ ተማሪ …
- … የመንፈስ ቅዱስ ማንነት እና ሥራውን ይረዳል ይህም በሚሰራ ወረቀት እና በፈተና ይታያል
- . . . መንፈስ ቅዱስ ለማምለክ፣ ሥጦታዎችን ለመለማመድ ተነሳሽነት በልቡ ይፈጠራል።
- . . . ስለ መንፈስ ቅዱስ ማስተማር፣ ሥጦታዎችን በድፍረት መለማመድ፣ በዚህ ዘመን ያሉትን ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች የመመዘን አቅም ያዳብራል።
የኮርሱ ዋና ማቴሪያ
- ለእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለጊዜ የሚሰጠው ሌክቸር የሚመሰረትበት ሐቲት
- ተጨማሪ መፅሐፍ : መንፈስ ቅዱስ ማንነቱ እና አገልግሎቱ. ዋልዶርፍ ጆን ኤፍ. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 1989
ከተማሪ የሚጠበቅ
- ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የተዘጋጀውን የእለቱ የማስተማሪያ ፅሑፍ እና ከተጨማሪ መፅሐፍ የተመደበውን አንብቦ መምጣት ይኖርበታል።
- የተሰጠውን የቤት ሥራ ሰርቶ በተባለው እለት ማስረከብ ይኖርበታል።
- በመጨረሻው የፈተና ቀን በመገኘት ፈተናውን ወስዶ ማለፍ ይጠበቃል።
ማርክ አሰጣጥ
የቤት ሥራ 40%
የመጨረሻ ፈተና 60%
የኮርሱ መርሃ ግብር
ቀን | የዕለቱ ርዕስ | የቤት ሥራ |
ፌብ 6 |
| ኖት 1 እና ዋልቮርድ ገፅ 1-52 |
ፌብ 13 |
| ኖት 2 እና ዋልቮርድ ገፅ 53-166 |
| ፌብ 20 |
| ኖት 3 እና ዋልቮርድ 7ፅ 180-206 ና240-248 |
| ፌብ 27 |
| ኖት 4 እና ዋልቮርድ ገፅ 209-239 |
| ማርች 6 የመጨረሻ ፈተና ቀን | ||
Curriculum
- 1 Section
- 0 Lessons
- 7 Hours
Expand all sectionsCollapse all sections
- THS103 Assignment 11

