የኮርሱ መግለጫ፡-
ይህ ኮርስ የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነትና ሥራ (ክርስቶሎጂ) እና ትምህርተ ድነት (ሰተሪዮሎጂ) መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ሥነ-መለኮታዊ ጥናት ያቀርባል። ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶችን፣ ታሪካዊ ዳህራና እድገትን በመርመር እና ክርስቶስ ማን እንደሆነ እና ለሰው ዘር ምን እንዳከናወነ የሚገልጸውን ሥነ-መለኮታዊ ጠቀሜታ ያብራራሉ። ለሥጋ መልበስ፣ ለስርየት፣ ለትንሣኤ፣ ለጸጋ፣ ለእምነት፣ ለጽድቅ፣ ለመቀደስ እና ለክብር ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ኮርሱ የተማሪዎችን እምነት ለማጠናከር፣ ሥነ-መለኮታዊ ግንዛቤን ለማጎልበት እና ለአገልግሎት፣ ለስብከት፣ ለማስተማር ብሎም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክር ለመስጠት የሚያስችል አቅም ይሰጣል።
የኮርሱ ዓላማ
የዚህ ኮርስ ዓላማ ተማሪዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ድነት ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ለመርዳት ሲሆን ይህም የወንጌልን መልእክት በግልጽ እንዲያቀርቡ፣ እውነተኛ የክርስትናን አስተምህሮ እንዲከላከሉ እና ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ሥነ-መለኮትን በአገልግሎት እና በዕለት ተዕለት ክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ እንዲተገብሩ ያስችላቸዋል።
ትምህርቱን በሚገባ ተምረው የጨረሱ ተማሪዎች፡
- የሥነ ክርስቶስን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ሥነ-መለኮታዊ መሠረቶችን ያብራሩ።
- የክርስቶስን ማንነት፣ አምላክነቱን እና ሰብአዊነቱን ጨምሮ ይረዳሉ።
- የክርስቶስን (ስርየት፣ ትንሣኤ እና ክብር) ትርጉም ፤ ሥራ እና ጥቐም ይረዳሉ።
- የተለያዩ የአስተምህሮተ ክርስቶስ ቀመሮችን መመርመር፣ መመዘንና በአመክንዮ መለየት ይችላሉ።
- የክርስቶስን ሥራና ማንነት በመገንዘብ በክርስቶስ የበለጠ የሚደነቁና እርሱን የሚያመልኩ ይሆናሉ።
- የሥነ ክርስቶስን እና የሶተሪዮሎጂ እውነቶችን ለስብከት፣ ለማስተማር፣ ለመምከር እና ለግል እምነት መተግበር የችላሉ።
- በዕምነታቸው ያድጋሉ፤ የላቀ ክርስቶሳዊ ምስክሮች ይሆናሉ።
Curriculum
- 4 Sections
- 0 Lessons
- 5 Weeks
Expand all sectionsCollapse all sections
- THS 102 የጽሁፍ ጥያቄ 11
- THS 102 የጽሁፍ ጥያቄ 21
- THS 102 የጽሁፍ ጥያቄ 32
- THS 102 ፈተና1
