የኮርሱ አጠቃላይ መግለጫ (Course Description)
ይህ የአራት ሳምንት መጽሐፍ ቅዱሳዊ የምክር አገልግሎት ኮርስ ምን እንደሆነ ፣ ለምን እንደሚያስፈልግ እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ እንዴት በተግባር እንደሚውል ለመማር የሚረዳ መግቢያ ነው።
በዚህ ኮርስ ውስጥ ፣ የሰዎችን የሕይወት ፈተናዎች እና ችግሮች በእግዚአብሔር ቃል (በመጽሐፍ ቅዱስ) እውነት ላይ ተመስርተን እንዴት መርዳት እንደምንችል እንማራለን ። ኮርሱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክርን መሠረታዊ መርሆዎች ፣ ውጤታማ የማዳመጥና የመግባባት ክህሎቶችን ፣ እንዲሁም ከተለመደው (ዓለማዊ) የስነ-ልቦና ምክር በምን እንደሚለይ በግልጽ ያስተምራል ።
ምክር መስጠት ለሚፈልጉ ፣ ለአገልግሎት መሪዎች ወይም ሰዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መርዳት ለሚፈልግ ማንኛውም ክርስቲያን ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ነው።
የኮርሱ አላማዎች (Course Objectives)
ተማሪዎች ይህንን ኮርስ ሲጨርሱ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
- የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክርን ምንነት መረዳት፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የምክር አገልግሎት ምን ማለት እንደሆነ እና በዛሬው ሕብረተሰብ ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት በግልጽ ማስረዳት።
- ልዩነቱን መለየት፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የምክር አገልግሎት እና በዓለማዊ የስነ-ልቦና የምክር አቀራረቦች መካከል ያለውን ዋና ዋና ልዩነቶች መረዳት ።
- የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ማወቅ፡ ሰዎችን ለመምከር የሚያስፈልጉትን ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ መርዎችንና ጥቅሶችን ለየተው ያውቃሉ ።
- ጥሩ አዳማጭ እና መካሪ መሆን፡ በምክር ወቅት ሰዎችን በጥቅስ ከማጣደፍ ይልቅ በቅንነት የማዳመጥ እና የመግባባት ክህሎትን ያዳብራሉ ።
- በተግባር ማዋል፡ የሰዎችን የሕይወት ፈተናዎች (እንደ ጭንቀቶች፣ የቤተሰብ እና የግንኙነት ችግሮች) በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ለመፍታት የመርዳት ብቃትን ያገኛሉ ።
ከተማሪ የሚጠበቅ
- ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የተዘጋጀውን የእለቱ የማስተማሪያ ፅሑፍ እና ከተጨማሪ መፅሐፍ የተመደበውን አንብቦ መምጣት ይኖርበታል።
- የተሰጠውን የቤት ሥራ ሰርቶ በተባለው እለት ማስረከብ ይኖርበታል።
- በመጨረሻው የፈተና ቀን በመገኘት ፈተናውን ወስዶ ማለፍ ይጠበቃል።
ማርክ አሰጣጥ
የቤት ሥራ 40%
የመጨረሻ ፈተና 60%