የኮርሱ መግለጫ (Course Description)
ይህ ኮርስ በቅዱሳት መጻህፍትና በነገረ-መለኮት ላይ በማተኮር የመጽሐፍ ቅዱስን የነገረ ፍጻሜ አስተምሮ (Eschatology) ዳሰሳ ይሰጣል። ተማሪዎች እንደ እግዚአብሔር መንግሥት፣ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት፣ የሺህ ዓመቱ መንግሥት፣ ትንሣኤና ፍርድ፣ እና እንደ አዲስ ስማይና አዲስ ምድር ባሉ ቁልፍ የፍጻሜ ጭብጦች በጥልቀት ይማራሉ። ኮርሱ መሰረታዊ የብሉይ እና የአዲስ ኪዳን ጽሑፎችን ይመረምራል፣ ዋና ዋና የትርጉም ማዕቀፎችን (ለምሳሌ፣ ቅድመ- ሺ አመት ፣ ድኅረ-ሺህ ዓመት እና ኢ-ሺ አመት)፣ እና የፍጻሜ ዘመን ነገረ-መለኮታዊ እና ሥነ-ምግባራዊ አንድምታዎችን ይዳስሳል። አፖካሊፕቲክ ጽሑፎችን በመተርጎም፣ ታሪካዊ ነገረ-መለኮታዊ እድገቶችን በመዳሰስ እና የፍጻሜ እውነቶችን በክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ፣ አምልኮ እና ተልዕኮ ላይ በመተግበር ላይ ልዩ ትኩረት ይደረጋል። ይህ ኮርስ የተዘጋጀው ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው የነገረ ፍጻሜ ትምህርት ለክርስቲያናዊ ህይወት እና አገልግሎት ያለውን ጠቀሜታና አስተዋፅኦ ለማሳየት ነው።
የኮርሱ ዓላማዎች (Course Objectives)
- የነገረ ፍጻሜን መሰረታዊ ጽንሰ–ሐሳቦች በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ይረዳሉ።
- ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ የነገረ ፍጻሜ ክፍሎችን በትክክለኛ የትርጓሜ መርሆች ማንበብ ይችላሉ።
- አፖካሊፕቲክ ቋንቋና ምልክቶችን በጥንቃቄ መተርጎም ይማራሉ።
- የክርስቶስ ዳግም ምጽአት እና የትንሣኤ ተስፋ በክርስቲያን ህይወት ላይ ያለውን ተፅእኖ ይገነዘባሉ።
- የመጨረሻ ዘመንን በተመለከተ የሚኖሩ ፍርሃቶችን እና ግራ መጋባቶችን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ተስፋ መመልስ ይችላሉ።
የኮርሱ አጠቃላይ ዝርዝር (Course Outline)
ክፍል 1፥ የመጨረሻ ዘመን ትምህርት መሰረታዊ ጽንሰ–ሐሳቦች (Eschatology)
- የመጨረሻ ዘመን ምንድን ነው? መቼ ተጀመረ? ይህን ማወቅ ለምን አስፈላጊ ነው?
- የመጨረሻ ዘመን ትንቢቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
- የመጨረሻ ዘመን ትንቢቶችን ለመረዳት የሚያስችሉ መርሆች
ክፍል 2፥ አፖካሊፕቲክ ጽሑፎች
- አፖካሊፕቲክ ጽሑፍ ምንድን ነው?
- የመጨረሻ ዘመን ምልክቶች እና አተረጓጎሟቸው (Signs of the End Times)
- የዳንኤል እና የራእይ መጻሕፍት እንዴት መንበብ እንደሚገባቸው እና ዳሰሳ
ክፍል 3፥ የመጨረሻ ዘመን ክስተቶች
- የክርስቶስ ዳግም ምጽአት እና “ንጥቀት” (The Second Coming of Christ & Rapture)
- ታላቁ የመከራ ዘመን (The Great Tribulation)
- የሺህ ዓመት መንግሥት (The Millennial Kingdom)
- ትንሣኤ እና የአለም ፍርድ (Resurrection and the Judgment)
- የአዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር (The New Heaven and New Earth)
ክፍል 4፥ የነገረ ፍጻሜ እና የክርስቲያን ህይወት
- የክርስቲያን ህይወት በነገረ ፍጻሜ ውስጥ (Living Eschatologically)
- ተስፋ፣ ታማኝነት እና ጽናት
- ነገረ ፍጻሜ እና ተልዕኮ
ከኮርሱ የሚጠበቀው (Expected Outcomes)
በኮርሱ መጨረሻ ላይ ተማሪዎች፡
- የመጨረሻ ዘመን ትንቢቶችን እና ክስተቶችን በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ይረዱታል።
- የመጨረሻ ዘመን ትንቢቶችን በእምነት እና በመንፈሳዊ ህይወት ውስጥ እንዴት እንደሚተገበሩ ይማራሉ።
- የመጨረሻ ዘመን ትንቢቶችን በተመለከተ የሚኖራቸውን ጥያቄዎች እና ግራ መጋባቶች ለመፍታት ይችላሉ።
- የመጨረሻ ዘመን ትንቢቶችን በተመለከተ የተጠናቀቀ እይታ እንዲኖራቸው ይረዳል።
የኮርሱ ምድቦች
- የክሬዲት ሰዓቶች፡ 3
- የቀጥታ ክፍለ-ጊዜዎች፡ 1 ጊዜ በሳምንት አርብ ምሽት (4 ጊዜ በወር)
- የጥናት ጊዜ፡ በሳምንት 3 ሰዓት
- የተማሪዎች የዕውቀት ግምገማ ፡ 2 ሳምንታዊ ጥያቄዎች (assignments) ከ40% የሚያዙ፣ አምስተኛው ሳምንት ላይ ደግሞ የመጨረሻ ፈተና ከ 60% የሚያዝ ይሆናል፡፡
የኮርስ መጸሐፍት
- Carson, D. A., and Brian J. Tabb, eds. All Things New: Revelation as Canonical Capstone. Downers Grove, IL: IVP Academic, 2019.
- Gladd, Benjamin L., and Matthew S. Harmon. Making All Things New: Inaugurated Eschatology for the Life of the Church. Grand Rapids, MI: Baker Academic, 2016.
Grudem, Wayne. Systematic Theology, 2nd ed. Grand Rapids, MI: Zondervan, 2020.
- Mühling, Markus. T&T Clark Handbook of Christian Eschatology. London: T&T Clark, 2015.
- Walls, Jerry L., ed. The Oxford Handbook of Eschatology. Oxford: Oxford University Press, 2008.
አማራጭ ይበልጥ ለማንበብ የሚያግዙ መጸሐፍት
- Wright, N. T. Surprised by Hope: Rethinking Heaven, the Resurrection, and the Mission of the Church. New York: HarperOne, 2008.
- Hoekema, Anthony A. The Bible and the Future. Grand Rapids, MI: Eerdmans, 1979.
Curriculum
- 4 Sections
- 0 Lessons
- 3 Hours
- ክፍል 1፥ የመጨረሻ ዘመን ትምህርት መሰረታዊ ጽንሰ–ሐሳቦች (Eschatology)0
- ክፍል 2፥ አፖካሊፕቲክ ጽሑፎች0
- ክፍል 3፥ የመጨረሻ ዘመን ክስተቶች0
- ክፍል 4፥ የነገረ ፍጻሜ እና የክርስቲያን ህይወት0
